Skip to content
Saturday, February 07, 2026
facebook
twitter
googleplus
dribbble
instagram
linkedin
የቤ/ጉ/ክ/መንግስት የዋና ኦዲተር መ/ቤት
የቤ/ጉ/ክ/መንግስት የዋና ኦዲተር መ/ቤት
መነሻ ገጽ
ሰለ እኛ
የቢሮ አደረጃጀት
ራዕይ፣ተልዕኮ፣እሴቶች
ተግባርና ሃላፊነት
ታርካዊ ዳራ
አገልግሎቶች
በመደበኛ ኦዲት ወቅት የአሰራር ግድፈት ወይም ጉድለት ከመገኘቱ የተነሣ አንድ ሂሣብ በልዩ ሁኔታ ኦዲት እንዲደረግ በምክር ቤቱ፤ በክልል ፍ/ቤቶች እና በሌሎች የመንግስት መ/ቤቶችና ድርጅቶች አማካኝነት የተጠየቀ እንደሆነ በጉዳዩ ክብደት ላይ ተመስርቶ የእቅዱ አካል በማድረግ ልዩ ኦዲት ያደርጋል፡፡
ኃላፊነቱን በተሟላ ሁኔታ ለመወጣት ይቻለው ዘንድ መጽሐፎችን፡ መዘክሮችን፡ መዝገቦችን፡ ሠነዶችንና ሌሎች መረጃዎችን ለመመልከትና አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ከህዝብ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት መረጃዎችን ዘገባዎችንና ትንተናዎችን ጠይቆ መቀበል ይችላል፡፡
አንድ ሂሣብ ወንጀል ባለበት ሁኔታና ታማኝነት በጐደለው አኳኋን መያዙን ለማመን ምክንያት ያለው እንደሆነ ይህንን ሂሣብ የሚመለከቱ ጹሁፎችን፣ መዘክሮችን፣ መዝገቦችን፣ ሰነዶችንና ከነዚህ ጋር ግንኙነት ባላቸው ሌሎች መረጃዎች ላይ በማሸግና በመመርመር ውጤቱን ለሚመለከተው ያሳውቃል
ከሚመለከታቸው መ/ቤቶችና ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለውስጥ ኦዲተሮች ተገቢውን ስልጠናና የሙያ ምክር ይሰጣል፣ እንደአስፈላጊነቱም የውስጥ ኦዲት ሪፖርት እንዲቀርብለት ሊያደርግ ይችላል
የኦዲት ውጤቱ ከፍተኛ ጉድለት መከሰቱንና ወንጀል መፈፀሙን የሚያሣይ ሆኖ ሲገኝ ይህንኑ ለክልሉ ፍትህ ቢሮ፣ለክልሉ መስተዳድር ም/ቤትና ለሥነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ይልካል፡
የክልሉ መንግሥት መ/ቤቶችና ድርጅቶች የገንዘብና ንብረት ሂሣብ አያያዝና አጠባበቅ አስመልክቶ በሚያዘጋጀው ማንኛውም ህጎች፡ደንቦችና መመሪያዎች ረቂቅ ሥራ ላይ አስፈላጊውን ምክርና አስተያየት ይሰጣል፣
በክልሉ ውስጥ በኦዲት ሙያ ለሚሰማሩ ኦዲተሮችና የሂሣብ አያያዝ ሥራ ለሚያከናውኑ ለኦዲትና የሂሣብ አዋቂዎች በስራው መስክ ለማሠማራት የሚያስችላቸውን የሙያ ብቃት የምስክር ወረቀት ይሰጣል፣ ያድሣል፣ ያግዳል፣ ይሰርዛል የሙያ ደረጃውን ጠብቀው ማከናወናቸውን ይከታተላል፡ ስልጠናና ምክር ይሰጣል፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም በህግ አግባብ ክስ ይመሰርታል
የክልሉ መንግስት መ/ቤቶችና ድርጅቶች ያስገኙት ውጤት ህጉን የተከተለ፤ ኢኮኖሚያዊ በሆነ አሠራር የተፈጸመ መሆኑንና ተፈላጊውን ግብ መምታቱን ለማረጋገጥ የክዋኔና የአከባቢ ጥበቃ ኦዲት ያደርጋል፤ ያስደርጋል፡፡
የክልሉ መንግስት መ/ቤቶችና ድርጅቶች አጠቃላይ የቁጥጥር ስርዓት በበቂ ሁኔታ መነደፉንና በትክክለኛ መንገድና በብቃት ተግባራዊ መሆኑን ለማረጋገጥ የሀብት ቁጥጥር ኦዲት ያደርጋል፤ ያስደርጋል፡፡
የክልሉን መንግስት መ/ቤቶችንና ድርጅቶችን ሂሣብ ኦዲት ያደርጋል፣ ያስደርጋል፤
የምስክር ወረቀቶችን በሚሰጥበትና በሚያድስበት ጊዜ በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጣ ደንብ የሚወሰነውን የአገልግሎት ዋጋ ያስክፍላል፡፡
ከዚህ በላይ በሠፈሩ ድንጋጌዎች መሰረት ያከናወነውን የኦዲት ሥራ ውጤት ሪፖርት አግባብ ላለው የመንግስት መ/ቤት ወይም ለድርጅት የበላይ ኃላፊ ያሳውቃል
ዳይሬክቶሬቶች
የፋይናንስና ህጋዊነት ኦዲት ዳይሬክቶሬት
የክዋኔ እና አካባቢ ጥበቃ ኦዲት ዳይሬክቶሬት
የኦዲት ጥራት ማረጋገጥ፣ ትምህርትና ስልጠና፣ ጥናት ምርምር ዳይሬክቶሬት
የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት
የመረጃ ዕቀድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት
የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
የሰው ሀብት አስተዳደር ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት
የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት
የስነ-ምግባር መኮንን
ሰነዶች
የአስር ዓመት መሪ እቅድ
የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ
አመታዊ እቅድ
አመታዊ ሪፖርት
አዋጆች
ደንቦች
መመሪያዎች
ሌሎች
ማህደርና ማስታወቅያ
ተንቀሳቃሽ ምስሎች
ምስሎች
ጨረታ
ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ
አግኙን
Search …
Menu Button
ሌሎች