በአንድ ቦታ ብቻ 21 ትሪሊዮን ኪዩቢክ ጫማ የጋዝ ክምችት ተገኝቷል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

.በአንድ ቦታ ብቻ 21 ትሪሊዮን ኪዩቢክ ጫማ የጋዝ ክምችት ተገኝቷል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ማዕድንና ጋዝን በተመለከተ ለምክር ቤቱ በሰጡት ማብራሪያ፤ የማዕድን ሥራችን በሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ውስጥ አንድ ከመቶ ድርሻ እየተጫወተ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
በተለይም የጋዝ ፕሮጀክት ባስጀመርንበት ሶማሌ ክልል አካባቢ ትልቅ ክምችት መኖሩን አስታውቀው፤ በአንድ ቦታ ብቻ 21 ትሪሊዮን ኪዩቢክ ጫማ የጋዝ ክምችት ኢትዮጵያ እንዳላት በሶስተኛ ወገን መረጋገጡን ጠቅሰዋል።
ይህንንም ሃብት ላለፉት ዓመታት ለምን መጠቀም አልቻልንም ብሎ ከመቆጨት ይልቅ አሁን ያለውን አውቆ በፍጥነት መጠቀም ከሁላችንም የሚጠበቅ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።
ከሁለት ዓመታት በፊት የጋዝ ፕሮጀክት የወሰደው አካል በበቂ መስራት ስላልቻለ ከቻይና መንግስት ጋር ተነጋግረን (GCG) ግሩፕ የሚባል ኩባንያ ጋር ውል ገብተን በ14 ወራት ውስጥ የመጀመሪያውን ዙር አጠናቀናል ብለዋል።
ጋዝ በኢትዮጵያ ውስጥ መምረት ይችላል የሚለው እሳቤ በመፈጠሩ ሁለተኛውን ዙር ጋዝ ለማምረት ሂደቱ ተጀምሯል፤ በ24 ወራት ተጠናቆ ሪፖርት ለምክር ቤት እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል።