(አሶሳ ፣ ግንቦት 8/2017 ዓ.ም) ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ዛሬ ባካሄደዉ የማኔጅመንት ስብሰባ 5 ሚልዮን የኮደርስ ስልጠና በተቀመጠዉ ደረጃ ለአመራሩና ባለሙያዎች በትኩረት እንደሚሰጥ እና ወቅቱ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በአግባቡ ለመምራት የዲጂታል ዕውቀት መዳበር እንዳለበት ክብርት ዋና ኦዲተሯ ለማኔጅመንት ሀሳብ በማንሳት በቀጣይ ቀናት ሁሉም የመ/ቤቱ ባለሙያዎች የኮደር ስልጠናዉን እንደሚወስዱ ገልፀዋል ።
ማኔጅመንቱም በቀረበው ሀሳብ ላይ በስፋት ከተወያዬ በኻላ አመራሩና ሁሉም የመ/ቤቱ ባለሙያዎች ቀጣይ ቀናት ስልጠናዉ ላይ በመገኘት በትኩረት መከታተል እንዳለባቸው ተገልፀዋል።
