መተከል ዞን ሥር ተሰማርተዉ የኦዲት ሥራ እየሰሩ ያሉ የመስክ ኦዲተሮች የክትትልና ድጋፍ ሥራዎች ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ፦ ክብርት ዋና ኦዲተር ወ/ሮ እናትነሽ ማሩ

መተከል ዞን ሥር ተሰማርተዉ የኦዲት ሥራ እየሰሩ ያሉ የመስክ ኦዲተሮች የክትትልና ድጋፍ ሥራዎች ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ፦ ክብርት ዋና ኦዲተር ወ/ሮ እናትነሽ ማሩ
( መተከል ፣ ጥቅምት 15/2018 ዓ.ም ) ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ እናትነሽ ማሩ መተከል ዞን በመገኘት በዞኑ ተሠማርተዉ የመስክ ኦዲት ሥራ እየሰሩ የሚገኙ ኦዲተሮች የክትትልና ድጋፍ ሥራ አከናዉነዋል።
በዉይይቱ የኦዲት ሥራዉ ጥራት ባለዉ ሁኔታ ፣ የተሻለ አፈጻጸም እንድኖር፣ የኦዲት ስነ-ምግባር በተላበሰ መልኩ ሥራዎች መሠራት እንዳለባቸዉ፣ ከኦዲት ተደራጊ ተቋማት ጋር ጤናማ የሆነ ሥራንና ሥራን ብቻ መሠረት ያደረገ ግንኝነት መኖር እንዳለበት ክብርት ዋና ኦዲተሯ ገልፀዋል።
በዉይይቱ ላይ የተገኙ ኦዲተሮች በበኩላቸዉ በበጀት ዓመቱ በመ/ቤቱ የተሠጣቸዉ ሥራ በአግባቡ በተሰጣቸዉ ጊዜ በዕቅድ መሠረት እንደሚሰሩ ገልፀዉ ፣ መንግስት በአሁኑ ወቅት ለመንግስት ሰራተኞች የጨመረው ደመወዝ በሥራቸው ላይ መነቃቃትን እንደፈጠረላቸዉ ተናግረዋል። የኦዲት ሥነ -ምግባርን በተላበሰ መልኩ እንደሚሰሩ መግባባት ላይ ተደርሠዋል።