የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት በበጀት ዓመት አንደኛ ሩብ ዓመት የተመዘገቡ አበረታች ውጤቶች ተጠናክሮ መቀጠል አለባቸዉ ፦ ክብርት ዋና ኦዲተር ወ/ሮ እናትነሽ ማሩ
(አሶሳ ፣ ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም )፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት የተከናወኑ ሥራዎችን ከመ/ቤቱ ሠራተኞች አባላት ጋር ገመገመ።
የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱ በመ/ቤቱ ዕ/ዝ/ክ/ግ/ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በወ/ሮ ጉደቱ ደበላ ቀርቦ ዉይይት ተደርጎበታል ።
የመ/ቤቱ ሠራተኞች በቀረበዉ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ በስፋት ተወያይተዋል፣ በአንደኛ ሩብ ዓመት ታቅዶ የተከናወኑ ሥራዎች አበረታች ዉጤት የተገኘበት መሆኑን ጠቁሞዉ እንደ ክፍተት ተብሎ በተለዩት ላይ ቀጣይ የዕቅድ አካል ሆኖ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
በመጨረሻም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ እናትነሽ ማሩ እንደገለጹት፣በአንደኛ ሩብ ዓመት የተከናወኑ አበረታች ዉጤቶች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለባቸዉ ገልፀዉ፣ በታዩት ክፍተቶች ላይ ቀጣይ የዕቅድ አካል ተደርጎ ትኩረት ተሰጥቶበት እንደሚሰራ ገልፀዋል።

Hi, this is a comment.
To get started with moderating, editing, and deleting comments, please visit the Comments screen in the dashboard.
Commenter avatars come from Gravatar.